
አዲስ አበባ፤ጥር 6/2017(ኢዜአ)፦የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሰራሮቹን ይበልጥ ለማዘመን ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ገለጹ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቢዝነስ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ፥ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቢዝነስ ልዑክ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ በዚህ ወቅትም ተቋሙ በሪፎርም ሂደት ላይ መሆኑን ገልፀው፥ የሚሰጡ አገልግሎቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማደራጀት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና ስራዎችንም ለማዘመን ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሁለቱ አካላት ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ይበልጥ ቀልጣፋ ከማድረግ አኳያ ልዑኩ ያለውን ልምድና ተሞክሮ በሚያጋራበት እንዲሁም በጋራ ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸው፥ ተቋሙ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ በትብብር ለመስራት ፋላጐት እንዳላቸው መግለጻቸውን ከአገልግሎቱ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025